
የመሀል ልጅ
.......ህይወት ትክ ብለህ ስታያት የምታስፈራ ናት፤ በሾኬ እና በጠረባ የተሞላች መሰናክሏ ብዙ...ዳገትና ቁልቁለቷ መዓት። ትክ ብሎ ላላያት አስመሳይነቷን ላልተረዳ ፤ማነኝ ምንድነኝ? ብሎ ዋጋውን ላልጠየቀ ፤ሆዱን ስትሞላለት ተመስገን ለሚልላት ምቹ ናት ።ጎርባጣው ጎረበጠኝ ካላልክ እኮ የሚመች ነገር አታስብም ።ካላሰብክ ደሞ ጎርባጣው ላይ ዝንትአለም ትተኛለህ፤ አይቆረቁርህም። የህይወት ሚስጥራ የመኖር ጥጉ ፤ክፋት ማንአለብኝነት ምን አገባኝ እና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ከሆነ ምንድነው የሰብዓዊነት ትርጉም? ካንተ ሃይማኖት ያልሆነን ሰው መውደድ ካልቻልክ ካንተ ዘር ያልሆነን ሰው ማክበር ካልቻልክ ለእኔ ልብ የሌለህ እና አእምሮ የሌለህ ቀፎ ነህ ! ከሁሉ በፊት ሰብዓዊነት ይቀድማል! ከዛ ቀጥሎ ስለ ሀገር ስለ ታሪክ ሃይማኖት ታወራለኛለህ .......እውነት ግን የቱ ነው የሚበልጠው? ኛ ሰው <ጦስህን ይዞት ይሂድ> የሚያውቀው ብርጭቆ ስትሰብር ብቻ ነው አንተ ስትወድቅ ግን <ብዬ ነበር> ይላል እንጂ ማንም እጁን ሰዶ ሊያነሳህ አይጥርም አይዞህ እኔም አልፌበታለሁ ማለት ክብሩን መሳት ይሆንበታል ። ደግመህ እንደማትንሰራራ እርግጠኛ ነው። ምፅ ብሎ በቁምህ ይቀብርሃል። ከትቢያ አራግፈህ ለመነሳት ትንፈራፈራለህ ምፅ ይሉልሀል ምፅ እናቱ ሞታ እኮ ነው ምፅ በጣም አንባቢ ስለነበር እኮ ነው ምፅ ካይሆኑ ሠው ጋር ገጥሞ እኮ ነው እያሉ በምፅ ሲፈራረቁብህ ፈሪ ትሆናለህ። የሚቀጥለውን እርምጃህን መቼም አታምነውም ወደኋላ ስታይ ግዜህ ይነጉዳል። በዚህ ሁሉ መሀል ህይወት እንደ ክፉ አስተማሪ መቅጣቷን አታቆምም። አይምሮህ ከገደብ በላይ ይሆንበታል ትደክማለህ በቃ ሰው ነሃ!! Product Details Synopses & Reviews ሴቶቻችን ከቅርብ