
ትዝታሽን ለእኔ ትዝታዬን ለአንቺ
ክዋክብታማ ሰማይ ለማየት መድፈሩ። የመጀመሪያዎቹ ገፆች ላይ ያሉት የትዝታ ቁርጥራጮች፣ እንደተቦዳደሰ ዘመናዊ ጂንስ የትውልድ ጭርንቁስ ጥፈትን የሚወክሉ መስሎኝ ነበር። ትንሽ የከረመ ፔሲሚዝም አለብኝ። በቫንጐ “Starry night” ተመስረኩዞ የመጣ ሌላ አጭበርባሪ ነበር የመሰለኝ። ምንም አዲስ ትርጉም ሲጠፋ፣ የምንምን ፍቺ ጥልቅ ለማስመሰል ከሚታሹት መሀል ነበር ይሄም መጽሐፍ መጀመሪያ የመሰለኝ። ትዝታ ቅንጭብጫቢ ስለሆነ፣ በቅንጭብጫቢ ድረታ ደረቴን ሊረግጠኝ መስሎኝ ነበር። ደግሞም፣ የመጀመሪያዎቹ አንቀፆች ላይ በነጠላ ሰረዝ አንድን ነገር ለመግለጽ የሚጨነቅባቸው ገፆች እውነትም ግልጽ አልነበሩም። ጭቶ እያከኩ አንድ ስፍራ ላይ ቆመው ወደፊት መራመድ አቅቷቸው ከሚብሰለሰሉት መሃል ግን አይደለም እሱባለው። እሱባለው እና እሱ እንዳለው የተፃፈው መጽሐፉ። ቀስ እያለ ነው ውበት የሚገለፀው። እንደ ኪዩቢዝም የተጣፉ የሚመስሉት ትዝታዎች በኋላ ላይ እየተሳሰሩ መምጣት ይጀምራሉ። ልክ እንደ ተፈጥሮ። ልክ እንደ "Butterfly effect” የቀደመው የድርሰቱ ገፆች ላይ የአተበው ትዝታ ውጤቱ በሂደት ነው የሚታወቀው። ነጣጥሎ ትዝታዎቹን ባያሳይ ለካ ሲገጣጠሙ ወጥ ምስል ባልፈጠሩ ነበር! እውነታ ከቁርጥራጭ “ከፒክስሎፕ” እንጂ ከወጥ ሽመና ተመዞ የሚዘረጋ አይደለም ለካ! Product Details Synopses & Reviews "የጥበብ ሰማይ ሊታረቅ ሲፈልግ ምልክቱን ያሳያል" ኂሳዊ ንባብ ፡ በደራሲ ሌሊሣ ግርማ (በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ነሐሴ 9 ቀን 2012 ዓ.ም እንዳስነበበው) እስክሪብቶዬን ያነሳሁት በሁለት እጄ ነው። ላንስሎት በድንጋይ ውስጥ ተሽጦ የኖረውን ምትሃታዊ ሰይፍ በሁለት እጁ መዞ እንዳወጣው። እያካበድኩ ሳይሆን የእውነት ብዕር ማንሳት እየ